አባል መሆን ለምን ያስፈልጋል?

  • የተቀላጠፈ ድጋፍ / ትብብር ስለሚያገኙ

በተሰማሩበት የስራ መስክ የሚያጋጥሞትን እንቅፋቶች ከሚመለከተው አካል ጋር በትብብር ለመፍታታት የሚያስችል በመሆኑ፣ የድጋፍ ደብዳቤ፣ የትብብር ደብዳቤ እንዲሁም በአካል ጉዳዮዎን በማሳወቅ የመፍትሄ አካል ስለሚሆን ኢዳማ ያስፈልጎዎታል፡፡

  • ኢንቨስትመንት ነክ መረጃዎች ስለምንሰጥ

መንግስት ዳያስፖራውን ለማነቃቃት ሲል የሚሰጣቸውን ማበረታቻዎች እየተከታተለ መረጃ ስለሚሰጥዎት፣ አመቺ የሆኑ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ስለሚነግርዎት፣ ወቅታዊና ታአማኒ የሆኑ የኢንቨስትመንት መረጃዎች በትኩሱ ስለምንሰጥዎ ኢዳማ ያስፈልጎዎታል፡፡

  • የማህበሩ ተሰሚነት ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመሩ

ኢዳማ ድምፁን ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍ አድርጎ የማሰማት አቅሙ እየጨመረ ይገኛል፡፡ የዳያስፖራውን ጥያቄዎች በማንሳት ቦታ እንዲሰጣቸው ጥረቱን በመጎልበቱ  ከማህበራችን ጋር በትብብር ለመስራት የሚሹ የግልም ሆነ የመንግስት ተቋማት ቁጥራቸው በርክቷል፡፡ ከፍ ያለው ድምፃችን ዳግም ከፍብሎ ይሰማል፡፡ ስለሆነም ኢዳማ ያስፈልጎዎታል፡፡

  • የእርስ በእርስ የልምድ ልውውጥ መፍጠር ስለሚቻል

በአባልነት የተመዘገቡ በርካታ ዳያስፖራዎች የዕውቀት፣ የክህሎት፣ የረጅም አመት የስራ ልምድ፣ የሐብትና የሀገር ፍቅር ባለቤቶች መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ይህን ከአንዱ ወደሌላው የሚተላለፍበትን፣ በመተባበር ፣ በመተጋገዝና አብሮ በመስራት የእርስበእርስ የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ አበክሮ ስለሚሰራ ኢዳማ ከመቼው ጊዜ በላይ ያስፈልጎዎታል፡፡

  • ጊዜዎት እና ሀብቶን ለመቆጠብ

ጊዜ ወርቅ ነው ከወርቅም በላይ፡፡ ይህን ጊዜዎትን በሚገባ ለመቆጠብና በአግባቡ ለመጠቀም፣ በዘመናት ያፈሯትን ሀብትዎን አንዳይባክንብዎት አሁንም ደግመን እንነግሮዎታለን ኢዳማ ያስፈልጎዎታል፡፡

  • የሚያጋጥምዎትን ችግር በጋራ ለመቅረፍ

ማንኛውንም ችግር በጥረት እንደሚፈታ ኢዳማ ያምናል፡፡  በጋራ ከሚደረግ ጥረት በግል ከሚደረግ ጥረት ይልቅ ውጤታማ ይሆናል፡፡ በግል ከሚጮኸው ይልቅ በጋራ የሚጮኸው ይበልጥ ይሰማል፤ ይደመጣል፡፡ ስለሆነም በጋራ ጥረት ችግርዎን ስለምንቀርፍ ኢዳማ ሆነኛ አጋርዎ ነውና ያስፈልግዎታል፡፡