DIASPORA DAY DIRECTIVE

 

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ቀን በዓል በአገር አቀፍ ደረጃ ለማክበር የወጣ ረቂቅ መመሪያ ቁጥር …/2007

በኢፌዲሪ የዳያስፖራ ፖሊሲ ሰነድ ላይ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ቀንን በቋሚነት በአገር አቀፍ ደረጃ ማክበር እንደሚያስፈልግ በግልፅ በተቀመጠው መሠረት የበዓሉን አከባበር ተፈጻሚ ማድረግ በማስፈለጉ፣

በዳያስፖራ ቀን በዓል  አከባበር  ላይ  የሚገኙ የዳያስፖራ አባላት በውጭ ከተለያዩ ምንጮች ይሰሟቸው የነበሩ  የተዛቡ መረጃዎች ትክክለኛ አለመሆናቸውን በአካል ተገኝተው እንዲያረጋግጡ ሁኔታዎችን ማመቻቸት በማስፈለጉ፣

መንግስት  ዳያስፖራውንና አገርን ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ  አዳዲስ አሰራሮችን  እንዲያወጣና ያሉትንም በመፈተሽ የማሻሻያ እርምጃ  እንዲወስድ የሚያግዙ ጠቃሚ ሃሳቦች በመድረኩ እንዲፈልቁ አስተዋጽኦ ያደርጋል ብሎ በማመን፣

የፌዴራልና የክልል መንግስታት፣ የግልና የማህበረሰብ ተቋማት እንዲሁም ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻና ተባባሪ አካላት ከዳያስፖራው ጋር በስፋት ተገናኝተው ዳያስፖራ ነክ መረጃዎችንና ሃሳቦችን ለመለዋወጥ እንዲችሉ አመቺ ሁኔታ ለመፍጠር ስለሚያግዝ፣

አገር  ውስጥ  የሚኖረው  ማህበረሰባችን  ስለ  ዳያስፖራው  ተሳትፎ  ምንነትና  አስፈላጊነት  እንዲሁም  በልማቱ  ውስጥ እየተጫወተ ያለውን ሚና እና መንግስት ለዳያስፖራው የሰጠውን ትኩረት   በአግባቡ እንዲገነዘብና የበኩሉን በጎ ድርሻእንዲወጣ መሠረት የሚጥል እንዲሆን ከግምት በማስገባት፣

ዳያስፖራው አገር ቤት በአካል ተገኝቶ ትውልድ አገሩ ውስጥ እየተደረገ ስላለው የልማት፣ የሠላምና የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እንቅስቃሴና በዚህ ረገድ እየተመዘገቡ ያሉ ለውጦችን/ውጤቶችን እንዲገነዘብና እንዲሁም በልማቱ ለመሳተፍ ያሉትን ዕድሎች እንዲያውቅ ሁኔታዎቹን ማመቻቸት እንደሚያስፈልግ በማመን፣

ከዚህ በፊት በአገር አቀፍ ደረጃ ለዳያስፖራው ከተዘጋጁ የውይይት መድረኮች የተገኙትን ተሞክሮዎች በማጤንና ከወቅታዊ የዕድገትና የልማት አቅጣጫ ጋር በሚጣጣም መልኩ በአገር አቀፍ ደረጃ የዳያስፖራ ቀን በዓል በቋሚነት ማክበር በማስፈለጉ፣

ይህ አገር አቀፍ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ቀን በዓል አከባበር መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

 1. 1. አጭር ርዕስ

ፍል አንድ ጠቅላላ

ይህ መመሪያ “የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ቀን በዓል አከባበር መመሪያ ቁጥር /2007” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

 1. ትርጓሜ

የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ፡-

 1. 1. “ዳያስፖራ” ማለት በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ አገር ዜጎች ማለት ነው፡፡
 1. “ትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ አገር ዜጋ” ማለት በትውልድ የኢትዮጵያ ዜግነት የነበረውና በአሁኑ ጊዜ በምርጫው የሌላ አገር ዜግነትን የወሰደ እና በአዋጅ 270/94 መሠረት የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የያዘ ሰው ማለት ነው፡፡
 2. 3. “ሚኒስቴር” ማለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማለት ነው፡፡
 1. 4. “ባለድርሻ አካላት” ማለት ሚኒሰቴሩ ዳያሰፖራውን አስመልከቶ በአዋጅ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ በቀጥታ ድጋፍና ዕገዛ የሚያደርጉ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ማለት ነው፡፡
 2. 5. “ተባባሪ አካላት” ማለት ሚኒስቴሩ ዳያስፖራውን አስመልክቶ በአዋጅ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ በተዘዋዋሪ መንገድ ድጋፍና ዕገዛ የሚያደርጉ ተቋማት ማለት ነው፡፡

6.“ሚሲዮን”  ማለት  በውጭ አገራት የሚገኙ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ፣ ቋሚ መልዕክተኛ፣ ቆንስላ ጄኔራል፣ የንግድ ጽ/ቤት ማለት ነው፡፡

 1. “አብይ ኮሚቴ” ማለት የዳያስፖራ ቀን በዓል አከባበር አካሄድን ከበላይ ሆኖ የሚመራና ሚኒስትሩ፣ የባለድርሻና ተባባሪ አካላት የበላይ ሃላፊዎች የሚገኙበት አካል ማለት ነው፡፡
 2. 8. “በዓል” ማለት በአገር አቀፍ ደረጃ የሚዘጋጅ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ቀን አከባበር በዓል ማለት ነው፡፡

9.በዚህ መመሪያ በወንድ ፆታ የተገለፀው የሴት ፃታን ያካትታል፡፡

 1. 3. የበዓሉ ዓላማ

በዓሉ የሚከተሉት አላማዎች ይኖሩታል፡፡

 1. 1. በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን በትውልድ አገራቸው እየተካሄዱ ስላሉ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች፣ የተመዘገቡ ውጤቶችን፣ የወደፊት አቅጣጫዎችን የማመላከት፣
 2. ዳያስፖራው በልማቱ ለመሳተፍ ያለውን ዕድል በተመለከተ ትክክለኛውን መረጃ ከምንጩ በተሟላ መልኩ አግኝቶ

አስፈላጊውን ግንዛቤ እንዲጨብጥ የማድረግ፣

 1. 3. ዳያስፖራው ከትውልድ አገሩ ጋር ያለውን ትስስር እንዲያጠናክር ሁኔታዎችን የማመቻቸት፣
 1. 4. የዳያስፖራው አባላት እርስ በእርሳቸው ማህበራዊ ግንኙነት እንዲፈጥሩ/እንዲያጠናክሩ/ እና የእርስ በእርስ ልምድ እንዲለዋወጡ የማድረግ፣
 2. 5. ዳያስፖራው በትውልድ አገሩ ልማት ውስጥ እያደረገ ያለውን ተሳትፎና በልማቱ ውጤት ውስጥ ያለውን ድርሻ በማሳየት የትውልድ አገሩ አጋዥ ሃይል ስለመሆኑ በራሱ በዳያስፖራውና ይበልጥኑ ደግሞ በመላው ህብረተሰባችን ዘንድእንዲታወቅ በማድረግ መነሳሳትን የመፍጠር፣
 1. 4. የበዓሉ ግብ

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ከትውልድ አገራቸው ጋር ያላቸውን ትስስር በማጠናከር በትስስሩ ራሳቸውም ተጠቅመው ለአገሪቱ ዕድገት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ማብቃት፤ እርስ በእርሳቸው ያሏቸውንግንኙነት ለማጠናከርና ዳያስፖራው በአገሩ ልማት በላቀ ደረጃ ሊሳተፍ የሚችልበትን ሃሳብ በማፍለቅ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲጫወት ማስቻል ነው፡፡

 1. 5. የተፈጻሚነት ወሰን

ይህ መመሪያ በአገር ቤት በአገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ቀን በዓል ብቻ የሚመለከት ሲሆን፣ እንደ ሁኔታው በውጭ አገራት የሚዘጋጅ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ቀን በዓል የሚመራበት መመሪያ ራሱን ችሎ የሚወጣ ይሆናል፡፡

 1. 6. የአብይ ኮሚቴው አደረጃጀት

ፍል ሁለት

ብይ ኮሚቴው አደረጃጀት፣ ውክልና፣ ስልጣንና ተግባር

የበዓሉ አከባበር አብይ ኮሚቴ የሚከተለው አደረጃጀት ይኖረዋል፡፡

 1. 1. ሚኒስቴሩ፣
 1. ባለድርሻ አካላት፣
 • የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣
 • 2. የኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣
 • 3. የትምህርት ሚኒስቴር፣
 • 4. የኢትዮጵያ ሴቶች፣ ወጣቶችና ህፃናት ሚኒስቴር፣
 • የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን፣
 • የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዬች ጽ/ቤት፣
 • የኢትዮጵያ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣
 • የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣
 • የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን፣
 • የኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን፣
 • የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣
 • የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣
 • ዘጠኙ የክልል መንግስታትና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች፣
 • የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበር እና ሌሎችም ሲሆኑ፣ እነዚህ ባለድርሻ አካላት ለፕሮግራሙ መልካም አፈፃፀም እንደየተቋማቱ ተግባርና ኃላፊነት የበኩላቸውን ሚና የሚወጡ ይሆናል፡፡
 1. 3. ተባባሪ አካላት፣
 • የአፍሪካ ህብረት ጽ/ቤት፣
 • የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን፣
 • UNDP፣
 • World Bank፣
 • IOM፣
 • CRDA፣
 • USAID፣
 • EU፣
 • የግሉ ዘርፍ ማህበራት፣
 • የሚዲያ ተቋማት፣
 • ታዋቂግለሰቦችና  ምሁራን  እና  ሌሎችም  ሲሆኑ፣  እነዚህ  ተባባሪ  አካላት  ለፕሮግራሙ  መልካም  አፈፃፀም እንደየተቋማቱ ተግባርና ኃላፊነት የበኩላቸውን ሚና የሚወጡ ይሆናል፡፡
 1. ውክልና

ሚኒስትሩ፣ ባለድርሻ አካላት እና ተባባሪ አካላት በአብይ ኮሚቴው ውስጥ በበላይ አመራሮቻቸው የሚወከሉ ሲሆን፣ አብይ ኮሚቴው እንደአስፈላጊነቱ በስሩ የተለያዩ ንዑሳን ኮሚቴዎችን አደራጅቶ ሊያሰማራ ይችላል፡፡

 1. 8. የአብይ ኮሚቴው ስልጣንና ተግባር
 1. 1. ሚኒስቴሩ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባር ይኖሩታል፡፡
 1. 1. ዓመታዊ አገር አቀፍ የዳያስፖራ ቀን በዓል አከባበር መነሻ እቅድና የድርጊት መርሃ-ግብር የሚመለከታቸውን አካላት በማሳተፍ እንዲዘጋጅና እንዲጸድቅ ያስተባብራል፡፡
 2. ሚሲዮኖች ለበዓሉአከባበር  ስኬት  የበኩላቸውን  ሚና  እንዲጫወቱ  አቅጣጫ  ይሰጣል፤  ድጋፍና  ክትትል

ያደርጋል፡፡

 1. 3. ከበዓሉ ዕቅድ ዝግጅት ጀምሮ እስከ አፈጻጸም ግምገማ ድረስ ያለውን አጠቃላይ የበዓሉን አከባበር ሂደት በሰብሳቢነት ይመራል፤ በዋና ፀሐፊነት ያገለግላል፡፡
 2. 4. ለበዓሉ አከባበር ማስፈፀሚያ በጀት ይመድባል፤ ከሌሎች አካላት ተጨማሪ ድጋፍ የማሰባሰብና ስራ ላይ የማዋል ስራ ይሰራል፡፡
 3. 5. ባለድርሻ እና ተባባሪ  አካላት  ለበዓሉ  አከባበር  ቁርጠኝነት  በማሳየትና  ትኩረት  በመስጠት  ለስኬታማነቱ እንዲንቀሳቀሱ ተልእኮ ይሰጣል፤ ይመራል፤ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፡፡

6.በዓሉን ምክንያት በማድረግ በውጭ እየኖሩም ሆነ ወደ አገር ተመልሰው ለትውልድ አገራቸው ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ  ላበረከቱ  የዳያስፖራ  አካላት፣  ድርጅቶች፣  ተቋማት፣  ወዘተ…  የማበረታቻ  እውቅና/ሽልማት የሚሰጥበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡

 1. የበዓሉን አከባበር ዝርዝር አፈጻጸም የሚመራና የሚፈጽም Event Organizer ቅጥር ያመቻቻል፤ የመግባቢያ

ስምምነት ይፈራረማል፡፡

 1. 8. ከአብይ ኮሚቴው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡
 1. የባለድርሻ አካላት ሥልጣንና ተግባር

የሚከተሉት ባለድርሻ አካላት የየራሳቸው ስልጣንና ተግባራት ይኖራቸዋል፡፡

 1. 1. የጠቅላይ ሚኒሰትሩ ጽ/ቤት
 • ጽ/ቤቱን በመወከል በበዓሉ አከባበር አካሄድ ላይ ሃሳብ ይሰጣል፤ አቅጣጫ ያስቀምጣል፡፡
 • የበዓሉን አከባበር ዝግጅት ሂደት በመከታተል ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሳውቃል፡፡
 • ክቡር ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ወይም ተወካያቸው በበዓሉ ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበልና ግብዣ እንዲያደርጉ፣ መልእክት እንዲያስተላልፉ ወይም ዳያስፖራውን በአገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንዲያወያዩ በቅርበት በመከታተል ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡
 1. የኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር
 • በአገራችን የቱሪዝም ኢንዱስትሪው እንዲጎለብትና ለኢኮኖሚያችን ተጨባጭ ድጋፍ እንዲያደርግ ስለቱሪዝም መስህቦቻችንና በመስኩ ያለንን ራዕይ፣ ዓላማና ግቦች ለዳያስፖራው በማስጨበጥ በተገቢው መልኩ ግንዛቤ መፈጠሩን ያረጋግጣል፡፡
 • በዘርፉ እየተደረገያለውን  እንቅስቃሴና  የተመዘገበውን  ውጤት  እንዲሁም  ዳያስፖራው  ሊሳተፍባቸው የሚችለውን ዕድሎች አስመልክቶ መረጃ ያዘጋጃል፤ ለዳያስፖራው ፍጆታ ያቀርባል፡፡
 • የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በባህላዊ ትዕይንት በበዓሉ ላይ እንዲቀርብና እንዲታይ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡
 • የአገራችንን የቱሪስት መስህቦችና ታላላቅ ፕሮጀክቶች የመስክ ጉብኝት ያመቻቻል፡፡
 • ከአብይ ኮሚቴው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡
 1. 3. የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር
 • በዘርፉ እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ፣ የተመዘገቡ ውጤቶችንና የወደፊት አቅጣጫዎችን አስመልክቶ መረጃ አዘጋጅቶ ለዳያስፖራው ፍጆታ ያቀርባል፡፡ በዘርፉ ከዳያስፖራው በሚፈለገው ድጋፍ ዙሪያ ያወያያል፡፡
 • ከአብይ ኮሚቴው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡
 1. 4. የኢትዮጵያ ሴቶች፣ ወጣቶችና ህፃናት ሚኒስቴር
 • በዘርፉ መንግስት እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ የተመዘገቡ ውጤቶችንና የወደፊት አቅጣጫዎችን አስመልክቶ መረጃ ለዳያስፖራው ፍጆታ ያቀርባል፤ ወያያል፡፡
 • ከአብይ ኮሚቴው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡
 1. 5. የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣
 • በዘርፉ እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ፣ የተመዘገቡ ውጤቶችንና የወደፊት አቅጣጫዎችን አስመልክቶ መረጃ አዘጋጅቶ ለዳያስፖራው ፍጆታ ያቀርባል፡፡
 • በዘርፉ ከዳያስፖራው በሚፈለገው ድጋፍ ዙሪያ ያወያያል፡፡
 • ከአብይ ኮሚቴው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡

6.የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣

 • በዘርፉ እየተደረገያለውን  እንቅስቃሴ፣  የተመዘገቡ  ውጤቶችን፣  የወደፊት  አቅጣጫዎችንና  በዘርፉ  ያሉ ዕድሎችን አስመልክቶ መረጃ አዘጋጅቶ ለዳያስፖራው ፍጆታ ያቀርባል፡፡
 • ከአብይ ኮሚቴው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡
 1. የንግድ ሚኒስቴር፣
 • በዘርፉ እየተደረገያለውን  እንቅስቃሴ፣  የተመዘገቡ  ውጤቶችን፣  የወደፊት  አቅጣጫዎችንና  በዘርፉ  ያሉ ዕድሎችን አስመልክቶ መረጃ አዘጋጅቶ ለዳያስፖራው ፍጆታ ያቀርባል፡፡
 • ከአብይ ኮሚቴው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡
 1. 8. የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ፣
 • የአገሪቱን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ፣ የተመዘገቡ ውጤቶችንና የወደፊት አቅጣጫዎችን አስመልክቶ መረጃ አዘጋጅቶ ለዳያስፖራው ፍጆታ ያቀርባል፡፡
 • በአገሪቱ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ዙሪያ ዳያስፖራውን ያወያያል፡፡
 • ከአብይ ኮሚቴው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡

9.የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

 • በዘርፉ እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ፣ የተመዘገቡ ውጤቶችንና የወደፊት አቅጣጫዎችን አስመልክቶ መረጃ አዘጋጅቶ ለዳያስፖራው ፍጆታ ያቀርባል፡፡ በዘርፉ ከዳያስፖራው ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ያወያያል፡፡
 • ከአብይ ኮሚቴው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡
 1. 1 የመንግስት ኮሙኒኬሸን ጉዳዮች ጽ/ቤት
 • በአገራችን የሚካሄደውንየሠላም፣  የልማትና  የዴሞክራሲ  ስርዓት  ግንባታ  ሂደት  መረጃ  ለዳያስፖራው እንዲደርስ ያደርጋል፡፡
 • በአገር ውስጥ በህዝባችን መካከል አንድ አገራዊ አመለካከት ለመገንባት ስለሚካሄደው የህዝብ ግንኙነት ስራ እንዲሁም በውጭ አገራት በፐብሊክ ዲፕሎማሲው ረገድ ልናሳካ ለምናስበው መልካም የአገራችን ገጽታ ግንባታ እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ መረጃ ለዳያስፖራው ያቀርባል፡፡
 • ከአብይ ኮሚቴው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡
 1. 11. የኢትዮጵያ መረጃና ደህንነት አገልገሎት
 • የአገራችንን ብሄራዊ ጥቅምና ደህንነት በመጠበቅ የውጭ ወዳጆችን ለማብዛትና በጠላትነት ሊያዩን የሚችሉ ወገኖችን አመለካከት ለመቀየር  ለሚደረገው  ዲፕሎማሲያዊ  ጥረት  መረጃ  በማቅረብ  በውጭ  ነዋሪው ማህበረሰብ ዘንድሚዛናዊ አመለካከት እንዲፈጠር እያደረገ ያለውን ዕገዛ አስመልክቶ መረጃ ያቀርባል፡፡
 • ዳያስፖራው ከዘርፉደረጃውን  የጠበቀ  የኮንሱላር  አገልግሎት  ማግኘት  እንዲችል  እየተደረገ  ያለውን እንቅስቃሴ፣ የተመዘገቡ ውጤቶችንና የወደፊት አቅጣጫዎችን አስመልክቶ ገለጻና ማብራሪያ ይሰጣል፡፡
 • ከአብይ ኮሚቴው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡
 1. 1 የኢትዮጵያ አየር መንገድ
 • በዘርፉ እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ፣ የተመዘገቡ ውጤቶችንና የወደፊት አቅጣጫዎችን አስመልክቶ መረጃ ያዘጋጃል፤ ለዳያስፖራው ፍጆታ ያቀርባል፡፡ ዳያስፖራውን ያወያያል፡፡
 • ከውጭ አገራት መጥተው በዓሉ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት የሚያሳዩ የዳያስፖራ አባላት ቅድሚያ አግኝተው የበረራ ቦታ ማግኘት የሚችሉበትን ሁኔታ ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ያመቻቻል፡፡
 • ከአብይ ኮሚቴው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡
 1. 13. የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን
 • የበዓሉ ቅድመ-ዝግጅት እንቅስቃሴ  በዳያስፖራው  በስፋት  እንዲታወቅ  የቅስቀሳና  የኘሮሞሽን  ሥራ በማስታወቂያ፣ በቃል ምልልስ፣ በዜና ወዘተ .. መልክ ለአየር እንዲበቃ ያመቻቻል፡፡
 • የበዓሉ የመክፈቻ እና የመዝጊያ ስነ-ስርዓቶች ቀጥታ የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ሽፋን እንዲያገኙ ሁኔታዎቸን ያመቻቻል፤ በዓሉ በዓለም አቀፍ ስርጭት እንዲኖረው ይሰራል፡፡
 • ከአብይ ኮሚቴው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡
 1. 14. የኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሸን
 • በዓሉ ደማቅና ትስስር ፈጣሪ እንዲሆን የተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች እንዲካሄዱ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡
 • ከአብይ ኮሚቴው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡
 1. 15. የፌዴራል/የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
 • የበዓሉ ሠላምና ጸጥታ እንዲከበር ከበዓሉ ዝግጅት ጀምሮ እስከፍጻሜው ድረስ የቅርብ ክትትል ያደርጋል፤ ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፡፡
 • የበዓሉን ተጋባዦች ዝርዝር መሠረት በማድረግ ተፈትሸው እንዲገቡ ያስተባብራል፡፡
 • ያልተጋበዙ የህብረተሰብ አባላት ከበር ላይ በመሰብሰብ የአካባቢውን ጸጥታ እንዳያውኩ አስቀድሞ የመከላከል ስራ ይሰራል፡፡
 • ከአብይ ኮሚቴው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡
 1. 16. ዘጠኙ የክልል መንግስታትና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች
 • በክልል እና ከተማ አስተዳደሮች የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም መስህብ ልማት ዕድሎችን እና አሰራሩን የተመለከተ መረጃ በማቅረብ ለዳያስፖራው ያስተዋውቃሉ፡፡
 • ዳያስፖራው በክልል እና ከተማ አስተዳደሮች በመኖሪያ ቤቶች ልማት እና ሌሎች ፕሮግራሞች ተጠቃሚ በመሆን አገሩንም እንዲጠቅም ለማነሳሳት የተዘረጉ ፕሮግራሞችንና አሰራሩን ለዳያስፖራው ያስተዋውቃሉ፤ ያወያያሉ፡፡
 • በየዘርፉና በየክልሉ ለልማቱ ልዩ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የዳያስፖራ አባላት እውቅና/ሽልማት እንዲበረከትላቸው ዕጩዎችን ለይተው ያቀርባሉ፡፡
 • ከአብይ ኮሚቴው የሚሰጣቸውን ሌሎች ተግባራት ያከናውናሉ፡፡
 1. 1 የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበር
 • ማህበር የተቋቋመበትን ዓላማ፣ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ፣ የተመዘገቡ ውጤቶችንና የወደፊት አቅጣጫዎችን አስመልክቶ መረጃ አዘጋጅቶ ለዳያስፖራው ፍጆታ ያቀርባል፡፡
 • የዳስፖራው አባላት በማህበሩ ጥላ ስራ እንዲሰባሰቡ የማነሳሳት ስራ ይሰራል፡፡
 • ከአብይ ኮሚቴው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡
 1. 3. የተባባሪ አካላት ሥልጣንና ተግባር

ተባባሪ አካላት ለበዓሉ ስኬት የሃሳብ፣ የፋይናንስ፣ የማቴሪያል፣ ወዘተ… ድጋፍ በማድረግ ትብብር ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡

 1. 4. የሚሲዮኖች ስልጣንና ተግባር
 • ዳያስፖራውንና በማሳተፍና የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ዳያስፖራው በበዓሉ ላይ በስፋት እንዲሳተፍ ዝርዝር መረጃውን በተለያዩ አግባቦች ያሳውቃሉ፡፡
 • ከበዓሉ መጠናቀቅ በኃላ ተሳታፊ የዳያስፖራ አባላቱ ወደመጡበት አገር ሲመለሱ መረጃውን በመጠቀም ግንኙነቱ እንዲጠናከር አስፈላጊውን ዕገዛ ያደርጋሉ፤ እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ መድረኮችን በማመቻቸት በኢትዮጵያ ቆይታቸው ያገኙትን ልምድ ለሌሎች የዳያስፖራ አባላት የሚያካፍሉበትን ሁኔታ ያመቻቻሉ፡፡
 • አገር ቤት ከሚከበረው በዓል በተጨማሪ በራሳቸው በሚያዘጋጇቸው ተመሳሳይ መድረኮች የዳያስፖራው አባላት እንዲሳተፉ ይሰራሉ፡፡ (ዝርዝር አሰራሩ ራሱን በቻለ መመሪያ የሚወሰን ይሆናል፡፡)
 • ከአብይ ኮሚቴው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡

ፍል ሶስት

ብይ ቴው አባላት ግንኙነት፣ የፋይናንስ ድጋፍና አጠቃቀም፣ የስራ ዘመን እና የስብሰባ ስነ-ስርዓት

 1. የሚኒሰቴሩ እና የባለድርሻና ተባባሪ አካላት ግንኙነት
 1. 1. ሚኒስቴሩ ለዳያስፖራ ፖሊሲ፣ ለዳያስፖራ አዋጅ እንዲሁም ደንብና መመሪያዎቸ ተጠሪ ይሆናል፡፡
 1. ሚኒስቴሩ የአብይ ኮሚቴው ሰብሳቢና ፀሐፊ ሆኖ ይመራል፤ ያገለግላል፡፡
 1. 3. ሚኒስቴሩ ለአብይ ኮሚቴ አባላት የሥራ ክፍፍል በማድረግና ተልእኮ በመስጠት የማስተባበር እንዲሁም ድጋፍና ክትትል የማድረግ ሚና ይጫወታል፡፡
 2. 4. ሚኒስቴሩ የክበረ በዓሉን ዕቅድ አፈጻጸምና የበጀት አጠቃቀም አጠቃላይ ሪፖርት አዘጋጅቶ ያቀርባል፤ በአብይ ኮሚቴው እንዲጸድቅ ያመቻቻል፡፡
 3. 5. ባለድርሻ እና ተባባሪ አካላት በአንቀጽ 10 ንዑስ አንቀጽ 2 ስለፋይናንስ ድጋፍ የተመለከተውን ተግባርና ሃላፊነታቸውን ይወጣሉ፤ በአብይ ኮሚቴው መደበኛ ስብሰባዎች ላይ በመገኘት የሥራ ድርሻቸውን ይወስዳሉ፤ የአፈጻጸም ሪፖርት ያቀርባሉ፡፡
 4. 1 አብይ ኮሚቴው ከባለድርሻና ተባባሪ አካላት ስለሚያገኘው የፋይናንስ ድጋፍና አጠቃቀም
 1. 1. አብይ ኮሚቴው የተጣለበትን ተግባርና ሃላፊነት በአግባቡ መወጣት ይችል ዘንድ በዋናነት ሚኒስቴሩ የራሱን በጀት ይመድባል፡፡
 2. ባለድርሻ እና ተባባሪ አካላት በዓሉን ለማክበር ከሚያስፈልገው በጀት የራሳቸውን ድርሻ በቀጥታ ድጋፍ መልክ የበጀት ድጎማ በማድረግ ወይም ከሌላ ምንጭ በማፈላለግ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ፡፡
 3. 11. የአብይ ኮሚቴው የሥራ ዘመን
 1. 1. የሚኒስቴሩ፣ የባለድርሻ እና ተባባሪ አካላት የበላይ አመራሮች በየጊዜው ሊቀያየሩ የሚችሉ ቢሆንም የአብይ ኮሚቴው የስራ ዘመን ላልተወሰነ ጊዜ ይሆናል፡፡
 2. 1 የስብሰባ ስነ-ስርዓት
 1. 1. አብይ ኮሚቴው መደበኛና አስቸኳይ ስብሰባ ይኖረዋል፡፡ መደበኛ ስብሰባው በየሁለት ወሩ የሚካሄድ ይሆናል፡፡
 1. ስብሰባዎች በየዓመቱ ከበዓሉ የዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ የበዓሉን መጠናቀቅ ተከትሎ እስከሚካሄደው የአፈጻጸም ግምገማ ድረስ ብቻ የሚዘልቅ ይሆናል፡፡
 2. 3. የሚኒስቴሩ፣ የባለድርሻ እና የተባባሪ አካላት ተወካዮች የበላይ አመራሮች ወይም ምክትሎቻቸው ብቻ መሆን

ይገባቸዋል፡፡

 1. 4. በማናቸውም የአብይ ኮሚቴው ስብሰባ ላይ ከአባላቱ ጠቅላላ ቁጥር ከግማሽ በላይ ከተገኙ ምልዓተ ጉባኤ ይሆናል፡፡
 1. 5. በማናቸውም የአብይ ኮሚቴው ውሣኔ ሊተላለፍ የሚችለው በስብሰባው ላይ የተገኙት አባላት ከግማሽ በላይ ሲደግፉት ነው፡፡

6.የአብይ ኮሚቴው ሰብሳቢ አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል፤ በተመሳሳይ የአብይ ኮሚቴው አባላት ከግማሽ በላይ ስብሰባ እንዲጠራ ከጠየቁ ሰብሳቢው ስብሰባ የመጥራት ግዴታ አለበት፡፡

ፍል አራት

ብይ ቴው ሰብሳቢ እና ጸሐፊ ተግባርና ሃላፊነት

 1. 13. የአብይ ኮሚቴው ሰብሳቢ ተግባርና ሃላፊነት
 1. 1. የአብይ ኮሚቴውን ስብሰባ ይጠራል፤ ይመራል፤ እንደአስፈላጊነቱ ንዑሳን ኮሚቴዎችን ያስተባብራል፡፡
 1. ለክብረ በዓሉ የሚያስፈልገውን በጀት ያዘጋጃል፤ ያስፈቅዳል፤ ከሌሎች ምንጮች ተጨማሪ ፋይናንስ የሚገኝበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡ ሲፈቀድም ከሚመለከታቸው አስፈጻሚ አካላት ጋር በመቀናጀት በስራ ላይ ያውላል፡፡
 2. 3. በአብይ ኮሚቴው ስለሚወሰኑት ውሳኔዎች መግለጫ ይሰጣል፡፡
 1. 4. ለበዓሉ ስኬታማነት በውጭ አገራት ስለሚሰሩ ስራዎች ለሚሲዮኖች አቅጣጫ ይሰጣል፤ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፡፡
 1. 5. የአብይ ኮሚቴውን የተጠቃለለ የአፈጻጸም ሪፖርት ያዘጋጃል፤ ያጸድቃል፡፡
 1. 14. የአብይ ኮሚቴው ፀሃፊ ተግባርና ሃላፊነት
 1. 1. ከሰብሳቢው ጋር በመመካከር የአብይ ኮሚቴውን አጀንዳ ቀርጾ ያቀርባል፤ የአብይ ኮሚቴውን ቃለ-ጉባኤ ይይዛል፡፡
 1. የአብይ ኮሚቴው ቃለ-ጉባኤዎችና ሌሎች ሰነዶች እንዲያዙና እንዲጠበቁ ያደርጋል፡፡
 1. 3. ከአብይ ኮሚቴው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡

ፍል አምስት

በበዓሉ ተሳታፊ ለመሆን መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

 1. 15. በበዓሉ ተሳታፊ ለመሆን መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
 1. 1. ማንኛውም ሰው የበዓሉ ተሳታፊ ለመሆን በውጭ አገር ነዋሪ የሆነ ወይም ተመልሶ በአገር ውስጥ በተለያዩ የስራ መስኮች ላይ የተሰማራ ኢትዮጵያዊ ወይም በትውልድ ኢትዮጵያዊ የውጭ አገር ዜጋ የሆነና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችልመሆን አለበት፡፡
 2. ማንኛውም የበዓሉ ተሳታፊ መሆን የሚችል ኢትዮጵያዊ ወይም በትውልድ ኢትዮጵያዊ በሚመለከተው አካል በኩል የተሳታፊነት ምዝገባ አካሄዶ የመግቢያ ወረቀት የያዘ መሆን ይኖርበታል፡፡
 3. 3. ማናቸውም ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች አካላት የጥሪ ደብዳቤያቸውን በመያዝና በማሳየት የበዓሉ ታዳሚ መሆን ይችላሉ፡፡

 

 1. 16. የበዓሉ አከባበር ጊዜ

ፍል ስድስት ልዩ ልዩ ጉዳዮች

 1. 1. በዓሉ በየዓመቱ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በነሐሴ ወር የመጀመሪያ ሁለት ሳምንታት ውስጥ የሚከበር ይሆናል፡፡
 1. በውጭ አገራት በሚሲዮኖች አማካይነት የሚከበረው በዓል የጊዜው ሁኔታ እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ የሚታይ ሆኖ ራሱን በቻለ መመሪያ የሚወሰን ይሆናል፡፡
 2. 1 መመሪያውን ስለማሻሻል

ይህ መመሪያ በሚኒስቴሩ የበላይ አመራር ውሣኔ በማንኛውም ጊዜ ሊሻሻል ይችላል፡፡

 1. 1 የመመሪያው ተፈጻሚነት

ይህ መመሪያ ከ                    ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

ቴድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር)

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር