DIASPORA COUNCIL DIRECTIVE

የዳያስፖራ አማካሪ ምክር ቤት ረቂቅ መመሪያ ቁጥር…/2007

 

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የዳያስፖራ ፖሊሲውን ለማስፈጸም በአገር ቤት በተለያዩ መስኮች ከሚሳተፉ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት የተውጣጣ አማካሪ ካውንስል እንደሚቋቋም በዳያስፖራ ፖሊሲው በመቀመጡ፣

መንግስት በዳያስፖራ ተሳትፎ ጉዳዮች ዙሪያ በሚያደርገው እንቅስቃሴ በቀጣይ ከአሰራር፣ ከአደረጃጀትና ከህግ ማዕቀፍ አንፃር ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባቸውን ጉዳዮች አስመልክቶ ዳያስፖራው የተደራጀና የተቀናጀ ገንቢ ሃሳብ እንዲያቀርብ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ጊዜው የሚጠይቀው ጉዳይ በመሆኑ፣

በመንግስትና  በዳያስፖራው  መካከል  ያለውን  ግንኙነት  በማሻሻል  የሃሳብና  የመረጃ  ልውውጥ  መድረክ  እንዲፈጠር ሁኔታዎችን ማመቻቸት በማስፈለጉ፣

በአጠቃላይ  ዳያስፖራውን  የሚያጋጥሙት  ችግሮች  በመንግስት  በኩል  ታውቀው  ሊወሰዱ  የሚገባቸውን  የመፍትሄ እርምጃዎች በተመለከተ ምክረ-ሃሳብ የሚቀርብበትን አሰራር መዘርጋት በማስፈለጉ፣

የዳያስፖራ  ተሳትፎ  ጉዳዮችን  አስመልክቶ  በዳያስፖራውና  በመንግስት  በኩል  በጋራና  በተናጠል  የሚሰሩ  ስራዎችን ለመለየትና የአተገባበር አቅጣጫ ለማስቀመጥ የሚያስችል መዋቅር መፍጠር በማስፈለጉና ለግንኙነቱም የአሰራርና የመተዳደሪያ ህግ መቅረጽ በማስፈለጉ፣

ይህ የዳያስፖራ አማካሪ ምክር ቤት ረቂቅ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

 1. 1. አጭር ርዕስ

ፍል አንድ ጠቅላላ

 1. 1. ይህ መመሪያ የዳያስፖራ አማካሪ ምክር ቤት ለመመስረት የወጣ መመሪያ ቁጥር  /2007˝ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
 2. ትርጓሜ

በዚህ መመሪያ ውስጥ የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም የማያሰጠው ካልሆነ በስተቀር፡-

 1. 1. “ሚኒስቴር” ማለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማለት ነው፡፡
 1. “ሚሲዮን” ማለት በውጭ አገር የሚገኝ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቲክ ኤምባሲ፣ ቋሚ   መልዕክተኛ፣ ቆንስላ ጄኔራል ወይም ንግድ ጽ/ቤት ማለት ነው፡፡
 2. 3. “ምክር ቤት” ማለት የዳያስፖራ አማካሪ ምክር ቤት ማለት ነው፡፡
 1. 4. “የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ አገር ዜጋ” ማለት የሌላ አገር ዜግነት ከመያዙ አስቀድሞ የኢትዮጵያ ዜግነት የነበረው ወይም ከወላጆቹ፣ ከአያቶቹ ወይም ከቅድመ አያቶቹ ቢያንስ አንዱ በማናቸውም ጊዜ የኢትዮጵያ ዜግነት ይዞ የነበረ የውጭ ዜጋ ሲሆን፣ በአዋጅ 270/94 መሰረት የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የያዘ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
 2. 5. “የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ” ማለት በአዋጅ 270/94 መሰረት የኢትዮጵያ ተወላጅ ለሆነ የውጭ አገር

ዜጋ የሚሰጥ መታወቂያ ካርድ ማለት ነው፡፡

6.“የበላይ አመራር” ማለት በሚኒስቴሩ ሚንስትሩ እና ሚንስትር ዴኤታዎች ማለት ነው፡፡

 1. በዚህ መመሪያ በወንድ ጾታ የተገለጸው የሴትንም ጾታ ያካትታል፡፡
 1. 3. የምክር ቤቱ ዓላማ

መንግስትና  ዳያስፖራው  በዳያስፖራው  ማህበራዊ፣  ኢኮኖሚያዊና  ፖለቲካዊ  ተሳትፎ  ጉዳዮች  ዙሪያ  የሁለትዮሽ የግንኙነት መስመር ለመዘርጋት ነው፡፡

 1. 4. መቋቋም

             ጀምሮ በአገር ቤት በተለያዩ መስኮች የሚሳተፉ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት አማካሪ ምክር ቤት ተቋቁሟል፡፡

 1. 5. የተፈጻሚነት ወሰን

ይህ መመሪያ በምክር ቤቱ በሚታቀፉ በአገር ቤት በተለያዩ መስኮች የሚሳተፉ የዳያስፖራ አባላት ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

 1. 6. የምክር ቤቱ አደረጃጀት

ፍል ሁለት

ር ቤቱ አደረጃጀት፣ ተግባርና ሃላፊነት እና ግንኙነት

ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ እና ፀሃፊ ይኖረዋል፡፡

 1. የምክር ቤቱ ተግባርና ሃላፊነት

ምክር ቤቱ ዓላማውን ለማሳካት የሚከተሉት ተግባራትና ሃላፊነቶች ይኖሩታል፡፡

 1. 1. ለዳያስፖራው ሁለገብ መብት፣ ግዴታና ጥቅም መከበር ከመንግስት ጋር ተቀራርቦ ይሠራል፡፡
 1. ለዚህም ቁልፍ ከሆኑ የዳያስፖራ አባላት እና አደረጃጀቶች ጋር ገንቢ ግንኙነት ይፈጥራል፡፡
 1. 3. የዳያስፖራውን ፍላጎቶችና ችግሮች እንዲሁም በመንግስት አሠራር ላይ ያለውን አመለካከት ለመለየት ከዳያስፖራው አባላት ጋር የቅርብ ግንኙነት በመመስረት መረጃ ያሰባስባል፤ ያደራጃል፡፡
 2. 4. የዳያስፖራውን ተሳትፎ ለማጎልበት በመንግስት በኩል የተዘረጉ አሰራሮች፣ አደረጃጀቶችና የህግ ማዕቀፎች መሻሻል

የሚገባቸው እንደሆነ ሲያምን የማሻሻያ ሃሳብ ያቀርባል፤ ምክር ይለግሳል፡፡

 1. 5. የዳያስፖራውን ሁለንተናዊ ተሳትፎ የበለጠ ለማጠናከር አዳዲስ ኘሮግራሞች መቀረጽ በሚችሉበት ሁኔታ ዙሪያ ሃሳቦቸን አደራጅቶ ያቀርባል፡፡

6.የዳያስፖራውን ተሳትፎ ለማጎልበት በመንግስት በኩል የተወሰዱ እርምጃዎችን፣ የተመዘገቡ ውጤቶችንና ያጋጠሙ

ችግሮችን በማጥናትና በመተንተን ለወደፊት ሊቀመጡ በሚችሉ አቅጣጫዎች ዙሪያ ምክር ይለግሳል፡፡

 1. መንግስት የዳያስፖራውን ተሳትፎ በማጎልበት ከትውልድ አገሩ ጋር ያለውን ትስስር እንዲያጠናክር አሰራር ዘርግቶ፣ አደረጃጀት ፈጥሮ እንዲሁም የህግ ማዕቀፎችን ቀርጾ ስራ ላይ ከማዋል አንጻር የሚወስዳቸውን እርምጃዎች ለመላው የዳያስፖራ አባላት ያሳውቃል፤ ግብረ መልሱን ተከታteሎ ለሚኒስቴሩ ያሳውቃል፡፡
 2. 8. መንግስት ዳያስፖራውን አስመልክቶ በሚያዘጋጃቸው እቅዶችና ኘሮግራሞች እንዲሁም በሚያደርገው የአፈጻጸም እንቅስቃሴ ላይ ተሳትፎ በማድረግ የድጋፍና የምክር አገልግሎት ይሰጣል፡፡

9.በአገራችን የእድገት ጉዞ ውስጥ ክፍተት በሚታይባቸው ዘርፎች ውስጥ በእውቀትና በቴክኖሎጂ ሽግግር ተሳትፎ በማድረግ ለልማቱ ልዩ አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ የሚችሉ የዳያስፖራ አባላትን በመለየት ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር እንዲገናኙ ሁኔታዎችን በማመቻቸት እንደ ድልድይ ሆኖ ያገለግላል፡፡

 1. 1 ዳያስፖራው አገሪቱ ለምታካሂደው የልማት፣ የሠላምና የዴሞከራሲ ሥርዓት ግንባታ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ በሰፊው የዳያስፖራ አባላት እንዲሁም በህብረተሰባችን ዘንድ ታውቆ ትክክለኛው ግንዛቤ እንዲጨበጥ ይሰራል፡፡
 2. 11. ዳያስፖራው የአገሪቱን ሠላምና ልማት በሚያደናቅፉና ብሄራዊ ጥቅማችንን በሚጎዱ ማናቸውም አይነት እንቅስቃሴ ውስጥ እንዳይገባ ምክር ይለግሳል፡፡
 3. 8. የምክር ቤቱ እና የሚኒስቴሩ ግንኙነት
 1. 1. በምክር ቤቱ እና በሚኒስቴሩ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያቀላጥፍ ከሚኒስቴሩ የሚወከል አገናኝ አካል ይኖራል፡፡
 1. አገናኝ አካሉ የምክር ቤቱ አባልም ሆነ ሠራተኛ አይሆንም፡፡
 1. 3. ምክር ቤቱ ከሚኒስቴሩ ጋር በዓመት አራት (4) ይገናኛል፡፡
 1. 4. ምክር ቤቱ ዓመታዊ ሪፖርት ለሚኒስቴሩ ያቀርባል፡፡
 1. 5. የሚቀርቡ ሪፖርቶች ምክር ቤቱ የተጣለበትን ሃላፊነት ለመወጣት ያደረጋቸውን እንቅስቃሴዎችና የተገኙ ውጤቶችን፣ የሚኒስቴሩን ግብና ዓላማ ለማሳካት የወሰዳቸውና ወደፊት የሚወስዳቸዉ እርምጃዎች፣ ሚኒስቴሩ ውሳኔ ሲያስተላልፍ ከግምት ሊያስገባቸው ይገባል የሚባሉ ጉዳዮችን እንዲሁም ሚኒስቴሩ ወደፊት በሚያዘጋጀው የራሱ ስትራቴጂክ ዕቅድ ውስጥ ቢካተቱ ይጠቅማል የሚላቸውን አዳዲስ ሃሳቦችን ያካትታል፡፡

6.ሚኒስቴሩ ዓመታዊ የዳያስፖራ ተሳትፎ ጉዳዮች ዕቅዱን እና የአፈጻጸም ሪፖርቱን በምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ ላይ በማቅረብ እንዲታወቅ ሊያደርግ ይችላል፡፡

 1. ሚኒስቴሩ በምክር ቤቱ ስብሰባዎች ላይ በመገኘት ያለ ድምፅ ሃሳብ ሊሰጥ ይችላል፡፡
 1. 8. ሚኒስቴሩ በሚያካሂዳቸው ዳያስፖራ ነክ የቦርድ ስብሰባ ላይ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ እንደአስፈላጊነቱ እንዲገኝ ሊፈቅድ ይችላል፡፡ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ በቦርድ ሰብሳቢው ሲፈቅድለት ያለ ድምጽ ሃሳብ ሊሰጥ ይችላል፡፡

ፍል ሶስት

ር ቤቱ ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ እና ፀሐፊ ተግባርና ሃላፊነት

 1. የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ተግባርና ሃላፊነት
 1. 1. የምክር ቤቱን ስብሰባ ይጠራል፣ በሊቀመንበርነት ይመራል፡፡
 1. የምክር ቤቱን የአፈጻጸም ሪፖርት ያዘጋጃል፤ ያፀድቃል፤ ለሚኒሰቴሩ ያቀርባል፡፡
 1. 3. ከሚኒስቴሩ ጋር ያለውን ግንኙነት ይመራል፤ ያስተባብራል፡፡
 1. 4. ከፀሐፊው ጋር በመመካከር የስብሰባው አጀንዳ ይቀርጻል፤ ረቂቅ አጀንዳው ላይ አባላት አስተያየት እንዲሰጡ ወይም ተጨማሪ አጀንዳ ካላቸዉ እንዲያስመዘግቡ ረቂቅ አጀንዳው እንዲደርሳቸው ያደርጋል፡፡
 2. 1 የምክር ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ ተግባርና ሃላፊነት
 1. 1. ለሊቀመንበሩ በማንኛውም ጊዜ የስራ ድጋፍ ይሰጣል፡፡
 1. ሰብሳቢው በማይገኝበት ጊዜ እሱን ተክቶ የሰብሳቢውን ተግባርና ሃላፊነት በተደራቢነት ይወጣል፡፡
 1. 3. ነባር ሰብሳቢው ስራውን ቢተው፣ በራሱ ፍቃድ ቢለቅ ወይም መስራት የማይችልበት ሁኔታ ላይ የሚደርስ ከሆነ እስከ ቀጣዩ አመታዊ ስብሰባ የመምራት ሃላፊነት ይወስዳል፡፡
 2. 4. እንደ አስፈላጊነቱ ንዑሳን ኮሚቴዎች እንዲመሰረቱ ይሰራል፤ ሲመሰረቱ ያስተባብራል፡፡
 1. 11. የምክር ቤቱ ፀሃፊ ተግባርና ሃላፊነት
 1. 1. ከሰብሳቢው ጋር በመመካከር የምክር ቤቱን አጀንዳ ቀርጾ ያቀርባል፤ የምክር ቤቱን ቃለ-ጉባኤ ይይዛል፡፡
 1. የምክር ቤቱ ቃለ-ጉባኤዎችና ሌሎች ሰነዶች እንዲያዙና እንዲጠበቁ ያደርጋል፡፡
 1. 3. ከሌሎች አካላት የሚመጡ ልዩ ልዩ ሪፖርቶችና ደብዳቤዎችን ይቀበላል፤ በየጊዜው ለሚደረጉ ስብሰባዎች ሪፖርት አዘጋጅቶ ለአመራሩ ያቀርባል፡፡
 2. 4. በምክር ቤቱ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡

ፍል አራት

 1. 1 አባልነት

ባልነት፣ የአባልነት መብትና ግዴታ

 1. 1. አባላት ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑና በውጭ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ሆነው አገር ውስጥ በተለያዩ ስራዎች ላይ ተሰማርተው የሚገኙ መሆን አለባቸው፡፡
 2. አባላት ዳያስፖራው በብዛት ከሚኖርባቸው አገራት የተወከሉ ቢሆን ይመረጣል፡፡ በዚህም ቢያንስ ግማሽ ያህሉ አባላት ዳያስፖራው በብዛት ከሚኖርባቸዉ አገራት መሆን አለባቸው፡፡
 3. 3. የአባላት ቁጥር ከ10 የማያንስ እና ከ25 የማይበልጥ መሆን አለበት፡፡
 1. 4. ሴቶች አባልነት ውስጥ እንዲኖሩ ይበረታታል፡፡ ከአባላት ብዛት ቢያንስ አንድ ሶስተኛው ቢሆኑ ይመረጣል፡፡
 1. 5. አባላት ስለዳያስፖራው አጠቃላይ  ሁኔታ  ግንዛቤ  ያላቸውና  ፍላጎቱን  በተገቢው  መልኩ  የሚገነዘቡ  እንዲሁም ዝግጁነትና ሙያዊ ችሎታ ያላቸው ቢሆን ይመረጣል፡፡

6.አባላት እንደአመቺነቱ በዳያስፖራው የሚመረጡ ይሆናል፡፡ ይህ ካልተቻለ ሚኒስቴሩ የራሱን መመዘኛ መስፈርት

በማስቀመጥ ሊሰይም ይችላል፡፡

 1. 13. የአባላት መብት
 1. 1. አንድ አባል በምክር ቤቱ እንቅስቃሴ ውስጥ ጥያቄ የማንሳት፣ ሃሳብና ድምፅ የመስጠት መብት አለዉ፡፡
 1. ሌላ የሚያግደው ምክንያት ከሌለ በስተቀር በምክር ቤቱ የመምረጥና የመመረጥ መብት አለው፡፡ ነግር ግን በራሳቸው ጉዳይ ላይ ድምጽ አይሰጡም፡፡
 2. 3. ማንኛውም አባል የምክር ቤቱን መተዳደሪያ መመሪያ የማግኘት መብት አለው፡፡
 1. 4. አንድ አባል በአሰራር ላይ የምክር ቤቱን አመራር በመጽሁፍና በንግግር የመተቸት መብቱ ያለገደብ የተጠበቀ ነው፡፡
 1. 14. የአባላት ግዴታ
 1. 1. አባላት በምክር ቤቱ  አሰራር  ውስጥ  የብዙሃኑን  ዳያስፖራ  አባላት  ፍላጎት  እንጂ  የራሳቸዉን  ማራመድ አይፈቅድላቸውም፡፡ የብዙሃኑ መብት ሲከበር የግልም አብሮ ይጠበቃል፡፡
 2. በምክር ቤቱ ማናቸውም መደበኛና አስቸኳይ ስብሰባዎች ላይ በቋሚነት የመገኘት ግዴታ አለባቸው፡፡
 1. 3. ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት መሳተፍ የማይችሉ ከሆነ አስቀድመው በጽሁፍ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
 1. 4. የምክር ቤቱን መመሪያ ማክበርና ማስከበር ይጠበቅባቸዋል፡፡
 1. 5. በተሟላ ስነ-ምግባርና ተጠያቂነት ማገልገል ይኖርባቸዋል፡፡
 1. 15. ከአባልነት መሰረዝ ወይም መሰናበት
 1. 1. አንድ አባል ራሱን ከምክር ቤቱ ማግለል ከፈለገ ከነምክንያቱ በፅሁፍ ምክር ቤቱን ያሳውቃል፡፡
 1. አባሉ ከምክር ቤቱ መርህና ዓላማ ውጭ የሆነ ድርጊት ሲፈጽም ወይም ምክር ቤቱን ለአደጋ የሚያጋልጥ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሆኖ ከተገኘ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አባሉ ሁኔታውን እንዲያስተካክል ይመክራል፤ ክትትል ያደርጋል፡፡ ይህ ውይይትና ክትትል ለውጥ ሊያመጣ ካልቻለ ሰብሳቢው አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት አባሉ እንዲሰናበት ለምክር ቤቱ አባላት በማቅረብ ሊያስወስን ይችላል፡፡
 2. 3. አባሉ በምክር ቤቱ 2 ተከታታይ ዓመታዊ ስብሰባዎች ላይ ያለበቂ ምክንያት ሳይሳተፍ ከቀረ በአባልነት ለመቀጠል እንዳልፈለገ ተቆጥሮ የሚሰናበት ይሆናል፡፡
 1. 16. የአባላት ክፍተት መሙላት
 1. 1. የአባላት ክፍተት ሲፈጠር በአንቀጽ 17 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 መሠረት አዲስ አባል በመምረጥ ወይም በመሰየም ሊሞላ ይችላል፡፡
 2. ተተኪው አባል ምክር ቤቱ የቀረው የስራ ዘመን እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚያገለግል ይሆናል፡፡
 1. 1 የምክር ቤቱ ምርጫ

ፍል አምስት

ር ቤቱ ምርጫ፣ የስራ ዘመንና የስብሰባ ስነ-ስርዓት

 1. 1. ምክር ቤቱ የራሱን ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ እና ፀሐፊ ይመርጣል፡፡
 1. በየሁለት ዓመቱ የሰብሳቢ ለውጥ ምርጫ ያካሂዳል፡፡
 1. 3. ምክር ቤቱ ምርጫዎቹን በራሱ ማሳካት ካልቻለ ሚኒስቴሩ እንዲሰይምለት ሊወክል ይችላል፡፡
 1. 1 የምክር ቤቱ የስራ ዘመን
 1. 1. ምክር ቤቱ የሶስት /3/ ዓመት የስራ ዘመን ይኖረዋል፡፡
 1. በዚህም አንድ አባል ከ2 ተከታታይ የስራ ዘመን በላይ ማገልገል አይችልም፡፡
 1. 3. አንድ አባል የስልጣን ዘመኑን አጠናቆ ከተሰናበተ ከአንድ አመት በኋላ ተመልሶ ሊመረጥ ይችላል፡፡
 1. 4. ሰብሳቢው ከ2 ተከታታይ የስራ ዘመን በላይ /በእያንዳንዱ የስራ ዘመን ከ2 ዓመት በላይ/ መስራት አይችልም፡፡
 1. 1 የምክር ቤቱ የስብሰባ ስነ-ስርዓት
 1. 1. የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ ቢያንስ በአመት አራት ጊዜ ይካሄዳል፡፡
 1. ስብሰባው የሚካሄድበት አጀንዳ፣ ሰዓትና ቦታ ከ15 ቀናት አስቀድሞ ለአባላቱ ይገለጻል፡፡
 1. 3. ከአባላት ከግማሽ በላይ ከተገኙ የስብሰባው ምልዓተ ጉባዔ እንደተሟላ ተወስዶ ስብሰባውን ማካሄድ ይቻላል፡፡
 1. 4. በምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ የሚኒስቴሩ ተወካይ አካል ሊገኝ ይችላል፡፡ ነገር ግን በሚተላለፉ ውሳኔዎች ላይ ሃሳብ የመስጠት በድምፅ አይሳተፍም፡፡
 2. 5. ምክር ቤቱ በሃሳቦች ላይ በተቻለ መጠን የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ ጥረት ያደርጋል፡፡ ይህ ካልተቻለ በአብላጫ

ድምፅ ይወስናል፡፡

 1. ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

ፍል ስድስት ልዩ ልዩ ጉዳዮች

 1. 1. ምክር ቤቱ የሚያቀርበው ሃሳብ አስፈላጊውን ፖሊሲ ለመቅረጽና ለማቀድ ዋጋ የሚሰጠው ቢሆንም የመፍትሄ ሃሳብ እንጂ የውሳኔ ሃሳብ ሊሆን አይችልም፡፡
 2. ሚኒስቴሩ የዳያስፖራ ተሳትፎ ጉዳዮችን ለመከታተል ስልጣን በአዋጅ የተሰጠው ስለሆነ ምክር ቤቱ የሚያቀርባቸው ምክረ-ሃሳቦች ተፈጻሚነት ላይ ትኩረት አድርጎ ይንቀሳቀሳል፡፡
 3. 21. በመመሪያው ውስጥ ያልተጠቀሱ ሌሎች ጉዳዮች

በዚህ መመሪያ ያልተጠቀሱና በየጊዜው ሊከሰቱ የሚችሉ አንዳንድ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ መመሪያው እስካልተጣሰ ድረስ አባላት ተወያይተው የሚሰጡት ውሳኔ ተፈጻሚነት ይኖረዋል፡፡

22.መመሪያውን ስለማሻሻል

ይህ መመሪያ በምክር ቤቱ እና በሚኒስቴሩ የበላይ አመራር ውሣኔ በማንኛውም ጊዜ ሊሻሻል ይችላል፡፡

 1. 23. የመመሪያው ተፈጻሚነት

ይህ መመሪያ ከ                    ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

ቴድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር)

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር